ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
33

የባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለተለያዩ ትም/ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የማሰልጠኛ ጥሬ ዕቃ ማለትም የኮንስትራክሽን እና የኤሌክትሪክ እንዲሁም የብረታ ብረት እቃዎች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የሚወዳደሩ ተጫራቾች በጨረታው የቫት ተመዝጋቢ ብቻ የሚወዳደር ይሆናል፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የማይመለስ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ጨረታውን ሲሞሉ በፖስተው ላይም ሆነ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታውን በሚሞሉበት ጊዜ በጨረታ ዋጋው ማቅረቢያ ላይ ምንም አይነት በነጠላም ሆነ በጥቅል ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  7. ጨረታውን በሚሞላበት ጊዜ በተጠየቀው መለኪያ መሰረት መሙላት ይጠበቅበታል፡፡
  8. እያንዳንዳቸውን እቃ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ3 ወር የሚቆይ (ቢድ ቦንድ) ወይም ለሚወደደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ በኮሌጁ ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ በጥቃቅን የሚወዳደሩ ከሆነ ከኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው የሚዘጋበት ቀናት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ይቆይና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ኮሌጁ ጨረታውን በጥቅልም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡
  14. በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ንብረቱን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ በሙያተኛ በማረጋገጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 218 0574 ደውለው መጠየቅ እና በፋክስ ቁጥር 058 218 05 78 መላክ ይችላሉ፡፡

ባሕር ዳር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here