ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
42

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የቢሮውን G+4 በአልሙኒየም የማከፋፈያ  በሮች እና የሳኒተሪ ስራ፤   የአልሙኒየም በር መስኮት መገጣጠም፣ የአልሙኒየም የግድግዳ መከፋፈል ስራ ላይ የተሰማሩ ደረጃ 8 በዘርፉ ፍቃድ ያላቸዉን ተቋራጮች ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰዉንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ ለመጫረቻ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችንና ማስረጃዎችን በማሟላት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ቀናት ድረስ አሟልታችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀን የሚያገለግል ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ ጋር ተያይዞ ኮፒና ኦርጅናል በሚል በሁለት ፖስታ በማሸግ ጨረታዉ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ተኛው ቀን 4፡00  ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00  ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን የጨረታ ሰነዱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታዉ በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ22 ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዥና ፋይ/ዳሬክተር ቢሮ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ለእድሳት ስራዉ የሚፈለገውን ማንኛዉም የግንባታ ቁሳቁስ ጥራት በቢሮ ባለሙያዎች ወይም መሃንዲሶች እየተረጋገጠ የሚሰራ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የቢሮውን የእድሳት ስራ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ50 ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 1800 ወይም 058 226 5397 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  13. ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here