የምሥ/ጐጃም ዞን ከፍ/ፍቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል 1. የውጭ ፈርኒቸር ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (ቲን) ያላቸው፡፡
- ከብር 200,000 እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የሚገዙት እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ የያዘ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ሰነድ ከምሥ/ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት ብር 50 (አምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃዎች ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ከግዥ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ከአሸነፈበት ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊው እቃዎችን ምስ/ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ቢሮ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ መቀነስም ሆነ መጨመር የምንችል መሆኑን እየገለጽን ነገር ግን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ በዚህ ያልተጠቀሱ በግዥ መመሪያው የተቀመጡ የተጫራቾች መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 55 50 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የምሥራቅ ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

