ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

የጨረታ ቁጥር 008/2018

የአብክመ በማእድን ሀብት ልማት ቢሮ በካፒታ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎችን የስነ-ምድር ጥናትና የካርታ ስራ እና የማእድን ፍለጋ ጥናት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠናት እና ካርታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ሎት የፕሮጀክቱ ስም         የሚጠናበት የጨረታ ማስከበሪያ
1 የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የስነ-ምድር ጥናትና ካርታ ስራ ፕሮጀክት፡፡ ወልቃይት        ወረዳው 60‚000
2 የኩታበር የስነ ምድር ጥናትና ካርታ ስራ ፕሮጀክት፡፡ ኩታበር       ወረዳው 30‚000
3 ሀብሩ  የስነ-ምድር ጥናትና ካርታ ስራ ፕሮጀክት፡፡ ሀብሩ       ወረዳው 40‚000
4 ደቡብ ወሎ የኦፖል ማእድን ጥናት ፕሮጀክት፡፡ አርጎባ 03 ጨምየ ጠቢሳ 50‚000
5 ሰ/ጎንደር ዞን የወርቅ ማእድን ጥናት ፕሮጀክት፡፡ ጠለምት ደረባና ነጋዴ መሻገሪያ ጥሉሳና ደረባ 55‚000
6 ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የብረት ማእድን ጥናት ፕሮጀክት፡፡ ቃፍታ ኢድሪስ ኢድሪስ 52‚000
7 ምስራቅ ጎጃም ዞ/ ድንጋይ ከሰል ማእድን ጥናት ፕሮጀክት፡፡ አዋበል አነቢ ጣቢት ገዳም 50‚000

 

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከላይ በሰንጠረዥ የተጠቀሰውን ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ለየብቻ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00  ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ  ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 0132/058 220 1087 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ/ ቀበሌ 07 ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት  ይገኛል፡፡

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here