ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
31

የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ የሚስፈልጉ ግብዓቶች ሎት1. ለምግብ አገልግሎት የሚዉል የተዘጋጀ በርበሬ፣ የተዘጋጀ ሽሮ፣ ጤፍ ወዘተ…፣ሎት2. ማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዠዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የእቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ከ1-2 ሎት ድረስ ከቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 ወይም በባንክ በተመሰረተ (ስፒኦ) ማቅረብ ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ ነጥብ አምስት ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ግ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል 16ኛው ቀን የስራ ካልሆነ ወደ ቀጣዩ የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  9. ጨረታው በእያንዳንዱ ፍላጎት በተናጠል ዋጋ ነው፡፡
  10. አሸናፊው በገባው ውል መሰረት እቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ ከተዘረዘረዉ ግዥ መጠን 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 4684 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here