የሐራጅ ጨረታ ማሰታወቂያ

0
19

አቶ ንጉሴ አለም ምስክር በፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ቅርንጫፍ የተበደሩትን ብድር በዉሉ መሰረት መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ አመላለስ በመያዧ የተያዘዉን በመያዧ ሰጨዉ በአቶ ንጉሴ አለም ምስክር ስም የተመዘገበ በፍ/ሰላም ከተማ 02 ቀበሌ በካርታ ቁጥር 471/2/2015 በአዋሳኝ በሰሜን ሀሚድ ሁሴን፣ በደቡበ አለባቸዉ አያሌዉ በምሥራቅ መንገድ እንዲሁም በምዕራብ ኡመር አሊ የሚዋሰንና የቦታዉ ስፋት 200 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት ግንቦት 22/2018 ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ባለዉ ጊዜ በመነሻ ዋጋ ግምት ብር 4,494,466 (አራት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና አራት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ስድስት ብር) ይጫረታል፡፡

የጨረታ ቦታ ፍ/ሰላም ከተማ ዋናዉ አደባባይ ከፍ ብሎ ከሚገኘዉ ፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ቅርንጫፍ ላይ ይሆናል፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋዉን ¼ ኛውን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ አያይዘዉ መቅርብ አለባቸዉ፡፡
  3. ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የሚጫረተዉ የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ፣ እንዲጫረት የሚፈቅድ ዉክልና እና ድርጅቱ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. ለመንግስት የሚከፈል ማንኛዉም ግብር ቫትን ጨምሮ እንዲሁም ከቦታዉና ቤቱ ዝዉዉር ጋር የተያያዘ ክፍያ በተጫራች በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፈያ ካለ ባንኩ የሚሸፍን ሆኖ ወደፊት ላለዉ ቀሪ ክፍያ ገዥዉ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊዉ ጨረታዉን ባሸነፈ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉን ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅና ቤቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
  7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 11 54 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here