የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2018 በጀት አመት 1ኛ. የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም 2ኛ. የተሽከርካሪ መኪኖች እና የጀኔሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግዥና /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 03/2018 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ግንቦት 04/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 08 64 99 67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ባሕር ዳር

