በአፈ/ከሳሽ ዘንጋና የገ/ቁ/ብ/ህ/ስ/ማህበር ኃ/የተወሰነ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ በጋሻው ቢታው መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ወ/ሮ አዳነች ሰውነት፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አብዩ እንዲሁም በደቡብ መንገድ ተዋስኖ የሚገኘው መኖሪያ ቤት በአቶ ቢተው ይሁን ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በመነሻ ዋጋ በብር 2,130,000 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር) ይሸጣል፡፡ ስለሆነም ከሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡-ተጫራቾች ወደ ጨረታው ሲመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዘው እንዲቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

