የንጎሮንጎሮ ጥብቅ አካባቢ

0
14

ንጎሮንጎሮ ጥብቅ ክልል በአፍሪካ አህጉር በታንዛኒያ ሰሜናዊ ቀጣና ነው የሚገኘው:: ጥብቅ ቀጣናው  እ.አ.አ በ1959የተመሰረተ ሲሆን በ1979 ከዱር አራዊት መጠለያነቱ ባሻገር በተፈጥሯዊ ድንቅነቱ እውቅና አግኝቷል:: በ2011  ቀጣናው ከ50 ሺህ በላይ የሆኑ ነባር የማሳይ ጎሳዎች መኖሪያነቱ የልዩ ባህል መገኛ ጥምር እውቅና አሰጥቶታል::

በእሳተ ገሞራ የተፈጠረ 30 ሺህ ሄክታር የሚሰፋው “ካልዴራ” ሰፊ ጐድጓዳ ቀጣና የጥብቅ ክልሉ ልዩ ገፅታ ነው:: የጥብቅ ክልሉ ስፋት 809440  ሄክታር ተለክቷል::ድንበሩም ከሰሜን ምእራብ የሰሬንጌቲ ብሔራዊ ፓርክ ሜዳዎች እስከ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ  ስምጥ ሸለቆ ይዘልቃል::በመልካምድራዊ አቀማመጡ በሳር ምድር እና ቁጥቋጦ የተሸፈነ ነው::

አርብቶ አደሮቹ ነባር የማሳይ ኗሪዎች ወደ ሰፊው የ “ካልዴራ” ወለል በሚኒራል የበለፀገ ግጦሽ መገኛ ከብቶችን በማሳማራት ኑሯቸውን ይገፋሉ:: በክልሉ 25 ሺህ የሚጠጉ የዱር እንስሳት ይገኛሉ፤ ከነዚህ ውስጥ በአካል ግዝፈት ካለቸው አንበሳ፣ ነብር፣ ዝሆን፣ ጎሽ እና አውራሪስ ተጠቃሽ ናቸው:: ክልሉ በዓለም የዱር እንስሳት ፍልሰት ተጠቃሽ ነው:: ከዓእዋፍ በእሳተ ጐሞራ በተፈጠሩት ማጋዲ፣ የናትሮን፣ ኢያሲ እና ኑዱቱ ኃይቆች የ “ፍላሚንጐ” ዝርያዎች በብዛት ይስትዋላሉ:: በአጠቃላይ 500  የዓእዋፍ ዝርያዎችን ይዟል- ጥብቅ ክልሉ:: በመልካምድራዊ አቀማመጡ በሳር ምድር ቁጥቋጦ የተሸፈነ ቀጣና ነው::

ወደ ጥብቅ ክልሉ በአውሮኘላን ከኬኒያም ሆነ ከኪሊማንጃሮ ዓየር ማረፊያ ተነስቶ መድረስ ይቻላል::

ለጥብቅ ክልሉ ዘላቂነት ህገወጥ አደን በስጋትነት መቀመጡን ድረገፆች አስነብበዋል::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ዩኔስኮ ድረ ገጽ አሲሊያ አፍሪካ እና አፍሪካን ወርልድ ሄርቴጅ ድረገፆችን ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here