በአፈ/ከሳሽ አቶ ሙሉአለም ታያቸው እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ደሳለው ሽቴ መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በግምጃ ቤት ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ግርማ አለማየሁ፣ በምዕራብ ተስፋየ ብዙአየሁ፣ በሰሜን የቀበሌ ቤት እንዲሁም በደቡብ መንገድ ተዋስኖ የሚገኘው በተከሳሽ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ በብር 732,360.05 (ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ብር ከዜሮ አምስት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ ስለሆነም ከሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ይሸጣል፡፡ ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳወቅን ውጤቱ ለግንቦት 28/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ለሆነው ቀጠሮ እንዲቀርብ ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

