- የጨረታ ዙር 2ኛ (ሁለተኛ)
- የጨረታው አይነት መደበኛ
- የአዲስ ቅዳም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 ከፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለድርጅት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከሚያዚያ 26/2018 ዓ/ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል ከአዲስ ቅዳም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከሚያዚያ 26/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 09/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ግንቦት 09/2018 ዓ/ም 11፡00 ይሆናል፡፡
- ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ግንቦት 10/2018 ዓ/ም ከረፋዱ በ3፡00 በአዲስ ቅዳም ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጋዜጣ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች ዝርዝር መግለጫ
| ተ.ቁ | የቦታው አድራሻ | የፕላን ምድብ | የተፈቀደው አገልግሎት | አዋሳኝ | የቦታው ኮድ ፓርስል ቁጥር | የቦታው ደረጃ | የቦታው ስፋት በካ/ሜ | የሊዝ መነሻዋጋ ለካ/ሜ | የግንባታው ከፍታ | ||||||
| ሰሜን | ደቡብ | ምሥራቅ | ምዕራብ | ||||||||||||
| ከተማ | ቀበሌ | ልዩ ስም | |||||||||||||
| 1 | አ/ቅዳም | 01 | ኳስ ሜዳ | ቅይጥ | ድርጅት | ፈ/ገበያ ማ/ል | መንገድ | አበባ ሽቱ | ማህበረ ቅዱሳን | CO-01 | 01 | 182.11 | 500 | G+0ና ከዚያ በላይ | |
| 2 | አ/ቅዳም | 01 | ኳስ ሜዳ | ቅይጥ | ድርጅት | እሱነው ደምሴ | መንገድ | ማህበረ ቅዱሳን | የጨረታ ቦታ | CO-02 | 01 | 169.39 | 500 | G+0ና ከዚያ በላይ | |
| 3 | አ/ቅዳም | 01 | ኳስ ሜዳ | ቅይጥ | ድርጅት | ሸማቾች | መንገድ | የጨረታ ቦታ | መንገድ | CO-03 | 01 | 241.4 | 500 | G+0ና ከዚያ በላይ | |
| 4 | አ/ቅዳም | 01 | መናኸሪያ | ድርጅት | ድርጅት | መናኸሪያ | መንገድ | መናኸሪያ | መንገድ | CO-04 | 01 | 1364.94 | 500 | G+2ና ከዚያ በላይ | |
የአዲስ ቅዳም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

