በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጣቁሳ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት መደበኛ በጀት በመኮንታ ቀበሌ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ እንዲገነባላቸው በጠየቁት መሰረት መ/ቤታችን ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የግንባታ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውን ተወዳዳሪዎች አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግንባታውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ተሸጦ በ22ተኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከጣቁሳ ወረዳ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ኦርጅናል እና ኮፒ የመጫረቻ ሰነዶችን ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሽግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በጣ/ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ 02 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ተጫራቾች የሚመረጡት ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ስለሆነ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገኙትን የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልጻፉ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘንብ በመሂ 1 ከጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ላይ በመክፈልና የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ሁሉንም የጨረታ ሰነዶች ፖስታው ላይ በማስገባት ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት የአንዱን ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ ፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈጻጸም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
የጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

