ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
21

የግዥ መለያ ቁጥር 32/2018 ዓ/ም

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ግንባታ አግልግሎት የሚውሉ አሸዋና ድንጋይ እንዲሁም ለተማሪዎች ቀለብ የሚውል ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. አድራሻ በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ ነዉ፡፡
  2. በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕረይዝ ስራ ክፍል በመዉሰድ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 001 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ የሚገዛዉ ዕቃ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ሆነው ለሚገዛው እቃ በQR COD በታተመ ደረሰኝ የሚስጥ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉባቸዉን ውል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ11 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ሰነዱን የወሰዱት ሁሉም ተጫራቾች ከመክፈቻ ቀን በፊት ሁሉም ከመለሱልን የመክፈቻ ቀን ሳንጠብቅ የምንከፍት ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 (ሰባት) ቀን በኋላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  10. ኢተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. አሸናፊዉ ድርጅት በግዥ መመሪያው መሰረት የቅድመ ግብር 3 በመቶ እና 15 በመቶ ቫት እንደሚቆረጥበት ታሳቢ ተደርጎ ዋጋውን መሙላት አለባቸው፡፡
  12. ኢንተርፕራይዙ ባወጣው ጨረታ ላይ 50 በመቶ የመቀነስ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 42 26 44 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here