ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
14

በምሥራቅ ጐጃም ዞን የስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለባለ በጀት ሴክተር መስሪያ ቤ/ቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1. የጽ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2. ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎችን፣ ሎት 4. የእንስሳት መገልገያ መሳሪያዎች እና ሎት 5. የአዳራሽ ወንበር ልብስ ሰፍቶ የሚያቀርብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ምዝገባ ያላቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ለሆኑ ግዥዎች (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችን መጠንና ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ለሎት ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር)፣ ለሎት 2. 20,000 (ሃያ ሽህ ብር)፣ ለሎት 3. ብር 3,000 (ሦስት ሽህ ብር)፣ ለሎት 4.ብር 2,000 (ሁለት ሽህ ብር) እና ለሎት 5. ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅ ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙበትን ሲፒኦ ወይም ደረሰኝ በተለየዩ ሶስት ፖስታዎች አሽገው ሶስቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ የመ/ቤቱን እና የአቅራቢውን ስምና አድራሻ በመጻፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን  ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ በማስገባት በዚህ ቀን ጨረታው ላይ ለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) ቢሮ ቁጥር 04 ከረፋዱ 4፡00 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው የሸነፈባቸውን እቃዎች ስናን ወረዳ በግዥ ጠያቂ መ/ቤቶች ንብረት ክፍል የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 288 01 22 /128 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ በሎት የሚያወዳድር ይሆናል፡፡
  14. በርክክብ ወቅት ለተጠቃሚ መ/ቤት ጥራቱን ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡

ማሣሠቢያ፡-

  • የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  • አድራሻችን ከደ/ማርቆስ ከተማ በ27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

የስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here