በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አማካይነት ከማ/ሰቡ እና ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች በተገኘ በጀት ጅ+3 ግንባታ ግራውንዱን ለማሰራት የግንባታ ማቴራል በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እስት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 3/2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የግንባታ ማቴሪያል ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው የሚለየው በሎት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከግንቦት 03/2018 እስከ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ ግንቦት 16/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግንቦት 16/2018 ዓ/ም 3፡30 ተዘግቶ በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች (ተወዳዳሪ) አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በፍጥነት ዕቃውን ማለትም የግንባታ ማቴራል በፍጥነት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የግንባታ ማቴራሉ በባለሙያ ታይቶ የምንረከብ መሆኑን እንገልፃለን በተጨማሪም ሲሚንቶ የምንረከበው በናሙናው መሰረት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት መረዳት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም፡፡
የቆላድባ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

