በፍ/ባለመብት ፀደይ ሆቴል የሚጣል እቁብ ማህበር እና በፍ/ባለ እዳ 1ኛ.ወ/ሮ ሽማጫሽ አንጀት፣ 2ኛ. አቶ ሀብታሙ መኮነን መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በሺንዲ ከተማ ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ የሚገኘውን የፍርድ ባለ እዳ ንብረት የሆነውን በአዋሳኙ፡- በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ታየች ዘለቀ፣ በስሜን እንዳለው አበበ እንዲሁም በደቡብ አለምነህ ሞላ መጠኑ 491 ካሬ ሜትር የሆነውን በካርታ ቁጥር 461/መ/ር/1 የተመዘገበ የግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 6,150,500 (ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ አምስት መቶ ብር) ሆኖ ሰኔ17/2018 ዓ.ም 4፡00 እስከ 7፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ የባለ እዳውን ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ የሸያጨ ገንዘብ ውሰጥ ቢቻል ሙሉን ካልተቻለ ¼ ኛውን በፍርድ ቤቱ በሞዴል 85 የሚያስይዝ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

