በአፈፃፀም ከሳሽ ሙላት ንጉሴ የሚጣል እቁብ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ 1ኛ. እንግዳ ዘለቀ፣ 2ኛ. ዘውዱ አበበ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ጉዳይ የአፈፃፀም ተከሳሾች የተወሰነባቸውን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት የአፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ክፍት ቦታ እንዲሁም በደቡብ አየሁ ፈንቴ መካከል ያለውን በአቶ እንግዳ ዘለቀ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,735,259.12 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ እንዲሁም 2ኛ. ተከሳሽ በአቶ ዘውዱ አበበ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ጠጀ ሙላት፣ በምዕራብ ሰለሞን ቁሜ፣ በደቡብ መንገድ፣ በሰሜን የሸ ቁሜ መካከል ያለውን መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,047,797.39 (አንድ ሚሊዮን አርባ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ከሰላሳ ዘጠኝ ሳንቲም) ፍ/ቤቱ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የጨረታውን ማስታወቂያ በጋዜጣ ለ30 ቀን እንዲውል በማድረግ የጨረታው ቀንም ሰኔ 18/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 እንዲሆን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት

