ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
32

ኢየሩሳሌም የሕፃናት እና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት የባሕር ዳር እና አካባቢዉ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት ያገለገሉ እና አዳዲስ የዉሃ ቧንቧዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲሁም ወንበርና ጠረጴዛዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡00 ድረስ የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የመወዳደሪያ ሰነድ ከዋናዉ መስሪያ ቤት አባይ ማዶ አጋር ሎጅ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘዉ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ለጨረታዉ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋዉን 20 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታዉ አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ዕለት ጀምሮ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ከፍሎ ማንሳት አለበት፡፡ በተጠቀሰዉ ቀን ዉስጥ ካላነሱ የጨረታዉ አሸናፊ ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሁኖ ንብረቱ ለ2ተኛ አሸናፊ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  4. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  5. ሁለትና ከዚያ በላይ ተጫራቾች ለአንድ ዕቃ እኩል ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ቢሆኑ እንደገና በማወዳደር አሸናፊዉ ይለያል፡፡
  6. የጨረታዉ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቹ ያሸነፈዉን ንብረት በተጠቀሰዉ መጠን ልክ ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡
  8. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉት ንብረት ዋጋ ሰነዱ ላይ ያለ ሥርዝ ድልዝ ገልፀዉ በመሙላት በታሸገ ኢንቭሎፕ ስም እና ሙሉ አድራሻቸዉን በመጥቀስ ከግንቦት 17/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም ድረስ ለድርጅቱ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታዉ ሰኔ 01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ  3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች በሚሰጡት ዋጋ ላይ ማስተካከያ ወይም ስርዝ ድልዝ ካደረጉ በተስተካከለዉ ፊት ለፊት መፈረም አለባቸዉ፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታዉ ሊሳተፍ አይችልም፡፡ በኮፒ ጨረታ ሰነድ መጠቀም አይቻልም፡፡
  11. በእርሳስ የተሞላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  12. በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ ፊርማ ከሌለበት ዋጋ አይኖረዉም፡፡
  13. አንድ ተጫራች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አይችልም፡፡
  14. ማንኛዉም ተጫራች በጨረታዉ ተካፋይ ሁኖ ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የሰጠዉን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
  15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 30 96 44 59 /09 18 76 49 03 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ አባይ ማዶ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ማራኪ ቀበሌ አጋር ሎጅ 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ከሞላ በኋላ በማሸግ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡በጨረታ ሰነድ ላይ ስምና ፊርማ በሚለዉ ክፍት ቦታ በሙሉ መፃፍና መፈረም ግዴታ ነዉ፡፡

ኢየሩሳሌም የሕፃናት እና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት

 የባሕር ዳር እና አካባቢዉ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here