የምሥራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚያሳትፍ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀተ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በመሂ 1 በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየጁቤ የመ/ደ/ሆስፒታል የግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ በማሸግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወይም /ህጋዊ/ ወኪሎቻቸው/ ባይገኙ ጨረታውን ለመክፈት የማያግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት፡፡ በተገለፀው የጊዜ ገደብ ያልቀረበ እና ውል ያልፈፀመ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል፡፡
- ውድድሩ በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ የሚለይ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃዎችን የጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ መሞያው ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለም ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 246 02 74 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

