በአፈ/ከሳሽ እንጅባራ ባጃጅ ተራ እቁብ ማህበር ሰብሳቢ አይሸሽም አሰጋ እና በአፈ/ተከሳሾች እነ አብርሃም ጥላሁን መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ 009፣ በምዕራብ 007፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ 013 የሚያዋስነው መኖሪያ ቤት በአቶ ደስታው ደምለው አለማየሁ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,694,056 (ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ሃምሳ ስድስት ብር) ይሸጣል፡፡ ጨረታው ከግንቦት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ 30 ቀናት ቆይቶ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡30 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

