ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የመደበኛ ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
19

የሞጣ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ እስክ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያና ለንግድ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ሞጣ ከተማ አስ/ መሬት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  3. ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ኘሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
  4. ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በሞጣ ከተማ አስተዳደሩ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ30 በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ሰነድ ከዋጋ እና ከሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ 058 661 20 40 /058 661 00 27 በመደወል መረጃ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሞጣ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here