ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
8

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የ2018 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የድርጅቱን ሃሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱ፡፡
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዪጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ካደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
  5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት በኢንተርፕራይዙ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ” ፣ “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከቀኑ በ 8፡30 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here