ግጭትን የመፍቻ ዘዴዎች

0
248

ግጭት ለሰው ልጆች አንዱ የሕይወት ገጽታ
ቢሆንም በአግባቡ ተይዞ መፍትሔ ሊበጅለት

ይገባል:: በአግባቡ ያልተያዘ ግጭት (unman-
aged conflict) ከፍተኛ ጉዳትን ያስከትላል።

ጉዳቱም ከንብረት ውድመት እስከ ክቡሩ የሰው
ሕይወት መጥፋት ሊደርስ ይችላል::
ግጭት መኖሩ ከታመነ ደግሞ የግጭት
መፍቻ መንገዶቹንም ቀድሞ ማበጀት ከምንም
በላይ አስፈላጊ መሆኑን የሚያስነብበው ቫላሚስ
(valamis.com) የተባለው ድረ ገጽ ነው።
ከችግሮች በመነሳት በተለያዬ መንገድ መፍትሔ
በማፈላለግ ለመፍታት የሚኬድበት መንገድ
እንዳለም መረጃው በመጠቆም እንደሚከተለው
ዘርዝሯቸዋል።
በቀዳሚነት የተጠቀሰው የችግር መፍቻ
መንገድ ተግባቦት /communication/ ነው።
ግጭትን የፈጠሩ አካላት በራሳቸው መንገድ
የየራሳቸውን የተለያየ ሃሳብ፣ ስጋት፣ ስሜት እና
እይታ (አመለካከት) እያነሱ ሲነጋገሩ በደንብ
ተደማምጠው ባለመግባባት እና ሃሳብን በአግባቡ
ባለመረዳት የሚፈጠሩ ችግሮች ሊቀንሱ ይችላል::
መተባበር (Collaboration) ደግሞ
በሁለተኛነት የተጠቀሰው የችግር መፍቻ መንገድ
ነው። ግጭቶች የሚነሱት አንድ የጋራ መዳረሻ
ኖሮ የተለያዩ ሃሳቦች ሲኖሩ በመሆኑ ለጋራ
መዳረሻ ሀሳብን አስተባብሮ ካሰቡት ቦታ ተባብሮ
መሥራትን እንደሚጠይቅ ድረ ገጹ ያስነብባል።
ሌላው የተጠቀሰው የመፍትሔ መንገድ

አስታራቂ ሃሳብን በጋራ ማቅረብ (Compro-
mising)ነው:: በዚህ ሂደት በግጭት መከሰት

መካከል ያሉ አካላት ሁሉንም ሊያስማማ
የሚችል ማዕከላዊ ሃሳብ ማቅረብ እንደሚገባ ነው
ምክረ ሀሳብ የሚያነሳው። በዚህ ሂደት ሁሉንም
የሚያረካ ነገር እና የተነሱበት ሃሳብ ባይሆንም
ተቀራራቢ ሃሳብን በማጣመር ለግጭቱ መቆም
የራስን አስተዋፅኦ ማበርከት ይችላሉ::
መረጃው እንደሚያመላክተው ሁሉም

አካላት ስሜታቸውን መቆጣጠር መቻል (Emo-
tional control) ወሳኝ ነው። በንግግር ውሥጥ

ስሜታዊ ሊያደርጉ የሚችሉ ሃሳቦች ቢኖሩም
ስሜት ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ መቆጣጠር
ትልቁ ኃላፊነት ነው:: በመጨረሻም ሃሳብን
ማወዳደር እና አሸናፊውን ሃሳብ በመምረጥ
መስማማት ያስፈልጋል::
እንደኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ሀገር በቀል
ባሕላዊ የግጭት መፍቻ መንገዶች ሰፊ ሽፋን
አላቸው:: ኢትዮጵያ የበርካታ ቋንቋዎች እና
ባሕሎች ባለቤት ናት:: እያንዳንዱ ማኅበረሰብ
የራሱ የሆነ አንጋፋ የግጭት አፈታት ሥርዓት
አለው:: ከተደራሽነት አንጻር ካየነው ደግሞ
ግጭት ሲነሳ መፍትሔ ለማግኘት ከሚኬድባቸው
ተቋማት ውስጥ መደበኛው ፍርድ ቤት ወይም
ከፊል ዳኝነት ስልጣን ያላቸው አካላት፣ ዘመናዊ
አማራጭ የግጭት መፍቻ ማዕከላት እና ባሕላዊ
የግጭት መፍቻ ዘዴን መጠቀም ዋነኞቹ ናቸው::
ባህላዊ አማራጭ የግጭት መፍቻ ሥርአትን
ካየን በማህበረሰብ እሴት ውስጥ በሁሉም
የሀገራችን አካባቢዎች ህዝቡ እንደ በጎ እሴት
የሚጠቀምባቸው እና ጎልብተው ለዘመናት
የዘለቁ በመሆናቸው ከተደራሽነት አንጻር እጅግ
ሰፊ ሽፋን እንዳላቸው የፌደራል አቃቢ ሕግ
በድረ ገፁ አስፍሯል::
ይህ ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት የሀገር
ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣
የየአካባቢው የጎሳ መሪዎች እንዲሁም በእነዚሁ
አካላት በሚመረጡ ሌሎች ሰዎች አሸማጋይነት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here