የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
11

በአፈፃፀም/ከሳሽ ዘንገና የገንዘብ ብ/ህ/ስ/ማህበር ተወካይ ማስረሻ አየነው እና በአፈፃፀም ተከሳሽ ያረጋል ገነት መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ  በእንጅባራ ከተማ፣ 02 ቀበሌ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አወቀ ሽፈራው፣ በሰሜን መለሰ የኔነህ  እንዲሁም በደቡብ በላይ መኮነን የሚያዋስነውን በአፈ/ተከሳሽ ያረጋል ገነት ስም የተመዘገበ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,460,755  (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ አምስት ብር) ስለሚሸጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኔ 15/2018 ዓ/ም እስከ ሀምሌ 15/2018 ዓ/ም ለ30 ተከታታይ ቀናት ድረስ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው  ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ማንኛውም ተጫራቾች በቦታው ተገኝተው መጫረት ይችላሉ ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ኛውን (ሲፒኦ) ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here