በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ሆቴል የሚጣል እቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ ታደለ ታረቀ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት የሆነው በሽንዲ ከተማ 01 ቀበሌ በምሥራቅ ገነቱ ጌታሁን፣ በምዕራብ ጌጡ ወለላው፣ በሰሜን በልስቲ ዋለ እና በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው የካርታ ቁጥር 1333 መ/ር የቦታው ስፋት 202.5 ካሬ ሜትር የሆነውን የአፈፃፀም ተከሳሽ መኖሪያ ቤት ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡30 መነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ (በዜሮ) መነሻ ዋጋ በጫረታ ይሸጣል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በጨረታ እንዲሸጥ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ትዕዛዝ የሰጠ ስለሆነ መኖሪያ ቤቱን በመጫረት መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ጨረታው የሚካሄደው ጥቅምት 10/2019 ስለሚሸጥ ከጠዋቱ 3፡30 አስከ6፡30 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ መጫረት ትችላላችሁ፡፡ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ ከተቻለ ሙሉውን ካልተቻለ ደግሞ 1/4 ኛውን ወዲያውኑ የሚያስይዝ መሆኑን እና ቀሪ ገንዘቡን ለጥቅምት 13/22019ዓ.ም በ4፡00 ለሆነው ቀጠሮ የምዕራብ ጎጃም ዞን ክፍተኛ ፍ/ቤት ችሎት ይዞ ቀርቦ መክፈል ያለበት መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል ፡፡
የም/ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

