ቋንቋ እና ዕድሜ

0
5

ብዙ ቋንቋ አቀላጥፈው የሚናገሩ ሰዎች በዕድሜ አቻ ከሆኑ አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የአንጐላቸው እርጅና ባመታት ያነሳ ወይም የጐለመሰ ሆኖ ሊገኝ እንደሚችል የሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ዘገባ ጠቁሟል፡፡

የአውሮፓ የነርቭ ሳይንስ ማህበራት ፌዴሬሽንን በመረጃ ምንጭነት የጠቀሰው ድረ ገጹ ብዙ ቋንቋዎችን መናገር የአንጐል እርጅናን በዓመታት እንደሚቀንስ አብነቶችን አስደግፎ አብራርቷል፡፡ በዚህም አራት ቋንቋ ተናጋሪዎች ከአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የአንጐላቸው እርጅና በ13 ዓመታት ያነሰ ይሆናል፡፡

በስፔን በባስክ የእውቀት ፣ የማገናዘብ ፣ የአንጐል እና ቋንቋ ጥናት ማዕከል ከሌሎች አራት አገራት ምርምር ማዕከላት ተመራማሪዎች ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት ለውጤት መብቃታቸውን ዶ/ር ሉሲያ አሞሩሶ ይፋ አድርገዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ 728 የናሙና ጥናት ተሣታፊዎችን የአንጐል እርጅና ለመገምገም የአንጐል የዕድሜ ልኬታ “ብሬይን ኤጂንግ ክሎክ” አመላካችን “ማግኔቶ ኢንሴፍላግራፊን” የተሰኘ መሣሪያን ተጠቅመዋል፡፡ መሣሪያውንም በተለያዩ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የአንጐል እንቅስቃሴ ልኬታ ለመተንተን ተገልግለውብታል፡፡

ከምርምሩ በተሰበሰበው ውጤት አመላካች መረጃ ሁለት ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ተመሳሳይ ዕድሜ ላይ ካለ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ስድስት ዓመታት፤ ሶስት ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ሰባት ዓመታት፤ አራት ቋንቋዎች የሚናገሩቱ በ13 ዓመታት እርጅናን ረተው ፣ ንቁ ሆነው ወይም ጐልምሰው መገኘታቸውን በማደማደሚያነት አስፍረዋል- ተመራማሪዎቹ፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here