ብርቅዬዎቹን ያደነችው – ታዳኝ

0
71

በኒውዝላንድ ለመጥፋት አደጋ የተጋለጡ በደርዘን የሚቆጠሩ ወፎችን በማደን ለቁጥራቸው መመናመን መንስኤ የዱር ድመት መሆኗ ተለይቶ ከሦስት ዓመታት ፍለጋ እና ክትትል በኃላ ብትገደልም ውዝግብ ማስነሳቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

በሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች “ናይን ላይቭስ” ዘጠኝ ህይወት የሚልቅፅል ስም የተሰጣት ድመት ከሌላ አካባቢ የተዳቀሉ “ፖቴክ” ወይም “ብራውንቴል” የተሰኙ 20  ወፎችን ፑሬሩዋ የተሰኘ ባህረገብ መሬት ላይ ለቀው ለማላመድ መንከባከብን ይቀጥላሉ፡፡ ሆኖም ከአንድ ሳምንት በኋላ አንዱ ተገድሎ ይመለከታሉ ከእለት እለትም የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ይገነዛባሉ፡፡

 

የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች በተለያዩ ቦታዎች ምስል ማንሻ ካሜራ ገጥመው ክትትላቸውን ይያያዙታል፡፡ አዳኟም ሴት የዱር ድመት መሆኗን ያረጋግጣሉ በካሜራ በተደረገ ክትትል ከተመለከቱት ምስል፡፡

ባለሙያዎች በየቦታው ወጥመዶችን አዘጋጅተው ሌት በጨለማ ሳይቀር ቢጠባበቁም ረዥዠም ሳር ውስጥ ገብታ እየተሽሎከሎከች ታመልጣለች፡፡

 

ድመቷ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የኪዊ ወፍ ዝርያዎችን፣  በአካባቢው  ብቻ  የሚገኝ  “ጌኮ”    የተሰኘ በቀጣናው ብቻ የሚገኙ እንስሳትን ማዳኗ ተረጋግጧል፡፡ ባለሙያዎቹ  በየወጥመዶች  እንዲሸታት እና እንድትገባ የተጠበሰ ዓሳ፣ ዶሮ እና ጥንቸል የመሳሰሉን በማንጠልጠል ባደረጉት ብርቱ ጥረት ለስኬት ይበቃሉ፡፡ የተጠበሰ ጥንቸል በተሰቀለበት ወጥመድ ውስጥ አዳኟ ድመት ገብታ ትያዛለች፡፡

ጉዳዩ በዚህ አላበቃም በወጥመድ የተያዘችውን ድመት ለሌሎቹ ስጋት እንዳትሆን በሚልም ባለሙያዎች በጥይት መተው ይገድሏታል፡፡ ይሄን የሰሙ የድመት አፍቃሪ እና የእንስሳት መብት  ተከራካሪዎች “ለምን ተገደለች? መገደል አልነበረባትም” በሚል ሙግት ማንሳታቸውን ድረ ገጹ በማደማደሚያነት አስነብቧል፡፡፡፡

 

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጳጉሜ  2 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here