ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የገዥ መለያ ቁጥር 05/2019 ዓ/ም

0
72

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ሎት1. የምግብ እህል አቅርቦት( ድፍን ጥሬ አተር)፣ ሎት2. የግንባታ ብረት ውጤቶች አቅርቦት (የጣርያ ኬንች ቲቦሳሪ ብረት RHS) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ) ብር ከሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርኘራይዝ ስራ ክፍል በመዉሰድ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢንተርኘራይዝ ቢሮ ቁጥር 001 የምትጫረቱትን የሰነዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ የሚገዛዉ ዕቃ ከ200,000 ብር (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ሆነው ለሚገዛው እቃ በኪው አር በታተመ ደረሰኝ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ ለሎት1 የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 100,000 (አንድ መቶ ሽህ) ብር፣ ለሎት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 100,000 (አንድ መቶ ሽህ) ብር በባንክ በተረጋገm ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒዩ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ11 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን
    በ4:30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል :: ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም ለጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  7. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከሰባት ቀን በኋላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ውል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሱ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት በግዥ መመሪያው መሰረት የቅድመ ግብር ሶስት በመቶ እንደሚቆረጥበት ታሳቢ ተደርጎ ዋጋውን መሙሉት ይኖርበታል፡፡
  10. ኢንተርፕራይዙ ባወጣው ጨረታ ላይ 50በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. አድራሻ በአዊ  አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ነዉ፡፡
  12. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 42 26 44 ይደዉሉ፡፡

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርኘራይዝ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here