የደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አላቂ የጽዳት ዕቃዎችንና የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት.1 አላቂ የጽዳት ዕቃዎቸን ፣ሎት2. የጽህፈት መሳሪያ ፤ ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና እቃዉ ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽ) ብር በላይ ከሆነ ቫት ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ወይም ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒዩ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሆስፒታሉ ህጋዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደልጊ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ04/01/2019 ዓ.ም እስከ 22/01/2019 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 3፡00 በሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ 3፡30 ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደልጊ ሆስፒታል ግዥ ፋይናስ ቢሮ በቀን 22/01/2019 ዓ.ም 4፡00 ላይ ይከፈታል ። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ድረስ መጥተዉ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ ያላስያዘና ውል ያልፈፀመ ከሆነ ግዥ ፈጻሚው አካል የጨረታውን ማስከበሪያ የመውረስ መብት ይኖረዋል።
- ክፍያው የሚፈፀመው በውሉ መሰረት ይሆናል ።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- በጨረታው ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደልጊ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ ።
- አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ወይም በዝቅተኛ ጥቅል ድምር ዉጤት ነዉ፡፡
የደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

