ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
40

በአብክመ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ፣ኮምፒዉተር እና ፕሪንተር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ  ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ስም፣አድራሻ የሚመለከተው ወይም ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡበት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሠከረት (ሲፒዩ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለ90 ቀናት አስገዳጅ የሆነ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች ከተሸነፋ ያስያዙት ቢድ ቦንድ እንዲለቀቅ በጸሁፍ ሲያሣውቁ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ስለ ትክክለኛ ስራ አፈጻጸም ዋስትና ያሸነፋበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ በሚቀጥለው 5 ተከታታይ ቀን  በሲፒኦ (ሲፒዩ)  ወይም በጥሬ  ገንዘብ በማስያዝ ውል ይፈጽማል፡፡ ዉል ካልፈጸመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ድረስ የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀዉ ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፤ በዚሁ እለት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  11. ተሸናፊው ተጫራቾች ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው ተለይቶ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  12. የጨረታ ዋጋ መሙያዉ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ከዉደድር ዉጭ ይደረጋል፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ሌሎች በዚህ መመሪያ ያልተገለጹ በጨረታ ሰነዱ እና በመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁ.144/2018 ተገዥ ይሆናል፡፡ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ ቁጥር 058 226 21 51/058 222 14 38፣ ፖ.ሣ.ቁ 1324.

የአብክመ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here