የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በ2019 በጀት አመት ለዋና ጠቅላይ መምሪያዉ በግዳጅ ላይ ለሚገኘው የክልሉ የፀጥታ ሃይል አገልግሎት የሚዉል ጋሌጣ ብስኩት በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ዉል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ ከ500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት የሚችል ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከምግብና መድሃንኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የታደሰ የጥራት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና ብስኩት የሚቀርብበትን ቦታዎች የሚገልጽ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀኖች ውስጥ ለእያንዳንድዱ ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል በአማራ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) በሲፒዩ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ከፈለጉ ማስረጃውን (የገቢ ደረሰኙን ) ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከፋይናንስ (ዋጋ ማቅረቢያ) ጨረታ ሰነድ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማችን በማሰፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ የአማራ ፖሊስ ዋናዉ መስሪያ ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከምሽቱ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡00 የሚዘጋ ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- የርክክብ ቦታው በተገለፀው የማቅረቢያ ቦታ ድረስ በግንባር የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 09 18 02 81 75/09 13 03 30 58 ባህር ዳር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት
ባህር ዳር

