የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ሎት1. ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 2. የተዘጋጁ ደንብ ልብሶች፣ ሎት5. ደንብ ልብስ ጫማ ፣ ሎት 04. የጽህፈት መሳሪያ፣ሎት5. ህትመት፣ሎት6. የፅዳት እቃዎች ሎት7. ልዩ ልዩ መገልገያ ፣ሎት8. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት9. የመኪና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና አግባብ ያለው ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ብር 500.000 ( አምስት መቶ ሽህ እና በላይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙት የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፌኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ከተጠቀሰው ስፔስፊኬሽን ውጭ ሰርዞ ሌላ ማስገባ ከውድድሩ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያዉን ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም በሚወጣዉ በኩር ጋዜጣ መመልከት ወይም ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በመገኘት በ50 (ሃምሳ ብር) በመግዛት መዉሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤታችን ዋና ገዥ በመ/ሂ፣ በመቁረጥ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ድረስ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይሁን እንጅ በጥሬ ገንዘብ ማስገባት አይቻልም። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒአ ከ1 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው አርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መስሪያ ቤታችን ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ከጥቅምት 2/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 11/2019 ዓ/ም ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰ/ጎን/ዞ ከፍ/ፍ/ቤት ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 በግልጽ ይከፈታል።
- አሸናፊው እቃዎቹን በሰ/ጎን/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል።
- የግዥ መጠኑ ከ20,000 ብር(ሃያ ሽህ ) በላይ ከሆነ ሶስት በመቶ ታክስ መክፈል አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፤ የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ በሞላው ዋጋ ሲሆን ተጫራቾች ሁሉንም ዝርዝር ዋጋ መሙላት አለባቸው፤ ያልሞላ ተጫራች ቢኖር ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም መሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የእቃዎችን ጥራት በተመለከተ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጥራቱን በማረጋገጥ ማስረከብ ግዴታው ነው፤ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ መሰረት የጥራት ችግር ያለባቸውን ሙሉ በሙሉ በመመለስ ትክከለኛ ጥራት ያላቸውን እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁ. 055 471 4941 ደውለው መጠየቅ
ይችላሉ።
የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ ቤት

