የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
3

በአፈ/ከሳሽ ቲሊሊ ሄርሜላ ሆቴል የሚጣል አፍሪካ የእቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሾች እነ አሳየ አይቸው (22) ሰዎች መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በአፈጻጸም ተከሳሽ በአቶ ሞሴ ታመነ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ፤ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 04 ፤ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ አለነ መንግስቱ፣ በምስራቅ እውነቱ ታመነ እንዲሁም በምእራብ ደረጀ አየሁ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው፤ መነሻ ዋጋው 2‚850‚000 (ሁለት ሚሊዬን ስምንት መቶ ሃምሳ ሽ ) ብር ሲሆን መነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ ይሸጣል፡፡ ጫረታው ከጥቅምት 10/2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 9/2019 ድረስ በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ፤ ህዳር 10/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡00 ቤቶች በሚገኙበት ቦታ መጫረት የምትችሉ ሲሆን፤ አሸናፊው ¼ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤት በፀደይ ባንክ አካውንት ገቢ እንዲያደርግ እና ቀሪውን በቀጠሮው ቀን ይዞ እንዲቀርብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም  መግዛት የምትፈልጉ በቦታው ተገኝታችሁ መወዳዳር የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ  አዝዟል፡፡

የአዊ/ብሔ/ዞ/ከ/ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here