ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 02

0
5

ሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከመደበኛ በጀት ሎት 1. መኪና እቃ እና ሎት 2 የመኪና ጎማና ባትሪ እቃ በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ግዥዉ የተጨማሪ እስቴ ታክስ የማይመለከተዉ ካልሆነ በስተቀር የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ በግብር ዓመቱ ተገቢዉን ታክስ እና የግብር ግዴታዉን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የወጣዉ ጨረታ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) ዋጋ በታች ከሆነ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅረብ ሳያስፈልግ  መወዳደር ይችላሉ፡፡ ከዚያ በላይ ከሆነ ግን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅርብ ያስፈልጋል፡፡
  3. ተጫራቾች ያሸነፉትን ሎት በተሰጠው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት በማቅረብና ማጓጓዝ፣ የመጫኛና የማዉረጃ ወጭዉን በራሳቸዉ መሸፈን አለባቸዉ ሁሉንም ንብረቶች በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ10 ( አስር ) ተከታታይ ቀናት ውል በመውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉበትን እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸው ማህተም ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ የአንዱ ዋጋ መዝለል ወይም ክፍት ማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በሰሜን ወሎ ዞን በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከነማስረጃዎቹ በታሸገ ፖስታ በድርጅትዎ ማህተም ተረጋግጦ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሁሉም ሎቶች ለተከታታይ 10ኛው ቀን በማዋል በ11ኛዉ  ቀን 5፡00 ላይ ታሽጎ 5፡30 በግዥ ንብረት አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ ሁሉም ጨረታዎች ወደ ቀጣይ የሥራ ቀን ተሸጋግሮ 5፡00 ታሽጎ 5፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  1. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላችሁ ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በደብዳቤ ማሳወቅ አለባችሁ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ሎት የመኪና እቃ ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) ሎት 2. የመኪና ጎማና ባትሪ እቃ ብር 9,000 (ዘጠኝ ሽህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የሚቀርበዉ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አይነት እንደተጫራቹ ምርጫ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ 10% በመቶ እንደተጫራቹ ምርጫ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በማስያዝ በጉ/ወ/ፍትህ/ጽ/ቤት በኩል ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑን መግለጽ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ የአንዱን ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ወይም በፍለድ ማጥፍት ከውድድር  ውጭ ያደርጋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኃላ የሚቀርብ ማስረጃና የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በጨረታዉ አከፋፈት ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ካልተገኙ ፖስታዉ በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  2. የበለጠ መረጃ ለማግኝት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 431 07 36 /033 540 07 21 ደውለው ወይም ጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here