የዳንግላ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የመሬት ማስተላለፍ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ መሠረት ለመኖሪያ እና ለድርጅት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን 1ኛ ዙር በግልጽ መደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለመኖሪያ እና ለድርጅት በመክፈል ዳንግላ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት ሰነድ መግዛት እና መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ እና መሸጫ ጊዜ ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው 10 የሥራ ቀናት ተቆጥረው በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሁሉም የጨረታ አስፈፃሚ ቡድን አባላት እና አግባብ ያለው አካል የሚሰይማቸውን ታዛቢዎች በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ዝግ ከተደረገበት ቀን በኋላ ባለው የመጀመሪያ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገው ምድር አዳራሽ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዳንግላ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቦታዎች በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች እና ቢሮ ቁጥር 07 ወይም በስልክ ቁጥር 058 221 07 72 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዳንግላ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

