ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
5

በሰሜን ወሎ ዞን የፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶች ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት 5. ብትን ጨርቅ፣ ሎት 6. ጫማ፣ ሎት 7. የመኪና መለዋወጫ እቃ እንዲሁም ሎት 8. የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ በሎት ድምር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ አገልግሎት መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዝጋቡ መሆናቸውን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉንና ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የእቃውን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለፍ/ገ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ህጋዊ ደረሰኝ መሂ ተቆርጦ ኮፒውን ወይም የጥቃቅን ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልግ የጨረታ የጥቃቅን ተጠቃሚ ከሆኑ ልዩ ድጋፍ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ቆይታ 10 ተከታታይ ቀናት ጥቅምት 09/2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም ቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱ ከፍላቂት ገረገራ ገንዘብ ጽ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች በአንዱ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም፡፡
  11. እንደ በጀት አቅም 30 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በእያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በሟሟላት ከጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ተዘግቶ ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  15. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበርያ 10 በመቶ ለፍ/ገ/ከአስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖርበታል፡፡ በተባለው ቀን ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  16. አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኋላ የአሸነፋቸውን እቃዎች በፍላቂት ገረገራ ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ያቀርባል፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 211 05 28 /033 2111 00 89 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here