ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
14

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ገንዘብ መምሪያ የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡- ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ ከነ ካላማዳሪው፣ ሎት 4. ኢንሹራንስ እና ሎት 5. የተሸርካሪ ቅባትና ዘይት ከመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡  ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የዋጋውን ጠቅላላ 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡
  7. ተወዳዳሪዎች የንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር አለባቸው፡፡
  8. የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ባንጃ ወረዳ ገንዘብና ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለጽሕፈት መሳሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለመኪና ጎማ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር)፣ ለሌሎች አላቂዎች ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ለኢንሹራንስ ብር 50,000. (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለተሸርካሪ ዘይትና ቅባት ብር 10,000 (አስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ደረሰኝ በመሂ/1 ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11 ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  13. አሸናፊ የምንለየው ጥራቱን የጠበቀ እቃ ካቀረቡት ውስጥ በየሎቱ በጠቅላላ ድምር በዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን ነው፡፡
  14. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፏቸውን እቃዎች ባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በባለሙያ እያስፈተሸ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  15. ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ባ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 06 47 /058 227 00 09 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. ጽ/ቤቱ እንደ ሴክተር መ/ቤቶች በጀት አቅም 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here