በቻይና የሚገኘው
የወረቀት አምራች ኩባንያ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን
ለማበረታታት በየዕለቱ
ለሚሮጡ ሠራተኞቹ በዓመቱ
መጨረሻ የገንዘብ ጉርሻ
እንደሚሰጥ ኦዲቲ ሴንትራል
ድረ ገጽ አስነብቧል::
በቻይና ጉዋንዶንግ ግዛት
የሚገኘው ወረቀት አምራች
ኩባንያ ላለፉት ዓመታት
በተለመደው መልኩ ዓመታዊ አፈፃፀምን መሠረት
ያደረገ ጉርሻ ወይም ሽልማት መስጠትን በመተው
ሠራተኞቹ በየዕለቱ በሩጫ በሚሸፍኑት ርቀት
መተካቱን ድረ ገጹ አስነብቧል:: ሠራተኞቹ በየዕለቱ
ምን ያህል ርቀት እንደሮጡ ከሚይዙት ሞባይል
መተግበሪያ አማካይነት ኩባንያው እንደሚመዘግብም
ነው የተለገፀው::
ኩባንያው ለአንድ ሠራተኛ በወር 50 ኪሎ ሜትር
ለሮጠ ሙሉ ደመወዝ፣ በወር 40 ኪሎ ሜትር ለሮጠ
60 በመቶ፣ 30 ኪሎ ሜትር ለሮጠ 30 በመቶ ጉርሻ
እንደሚሰጥም ነው የተገለፀው::
የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ኩባንያው
የጀመረው አዲሱ ማትጊያ “በአንድ
ድንጋይ ሁለት ወፍ” ሲሉ ለሠራተኞች
ጤናንም ገንዘብንም ማስገኘቱን ዘግበዋል::
በሌላ ወገን አንዳንድ ሠራተኞች “የለም
ሠራተኞችን የሚለያይ ነው” ሲሉ
ተችተዋል:: ለዚህም ሠራተኞች አቅም
ያላቸውን ከሌላቸው፣ የጤና ሁኔታ
ልዩነቶችን ከግምት ውስጥ ያስገባ
አለመሆኑን በመከራከሪያ ነጥብነት በድረ
ገጽ ላይ በሰፈሩት አስተያየት አንስተዋል::