በጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

0
192

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2016 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀትና በውስጥ ገቢ የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም 1. የጽሕፈት
መሳሪያ እቃዎች፣ 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 3. ህትመት፣ 4. የጽዳት እቃዎች፣ 5. የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ 6. የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ 7. የስፖርት መምህራን ትጥቅ፣ 8. የሕንጻ መሳሪያ
እቃዎች፣ 9. የቧንቧ ውሃ እቃዎች፣ 10. የስፖርት ማሰልጠኛ እቃዎች፣ 11. የሠራተኞች የደምብ ልብስ ማለትም ብትን ጨርቅ፣ ጫማ፣ ሸሚዝ እና ካፖርት ወዘተ… እና 12. የአጸደ ህጻናት መጻሕፍት
በግልጽ ጨረታ ዘዴ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተወዳዳሪዎች የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ኮሌጁ ከ20,000.00 /ከሃያ ሽህ ብር/ በላይ ግዥ ሲፈጽም መንግሥት በሰጠው ውክልና መሰረት 7.5 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
5. ኮሌጁ ከ10,000.00 /ከአስር ሽህ ብር/ በላይ ግዥ ሲፈጽም ሁለት በመቶ የዊዝሆልዲንግ ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
6. በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው እቃና ቁጥር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች ይህ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ዋና
ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
10.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም
በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው፡፡
11.ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ተገልጾላቸው ያሸነፉትን ዕቃ ጠቃላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲ.ፒ.ኦ./ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና
ወይም በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ዋናውን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው
ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 4፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
13.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ታሽጎ በ4፡
35 ይከፈታል፡፡
14.ውድድሩ በተናጠል የምናወዳድር መሆኑን ተወዳዳሪዎች ሊያውቁት ይገባል፡፡
15.አሸናፊዎች እቃዎቹን ኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ንብረት ክፍል ገቢ በማድረግ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
16.ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
17.በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 141 00 31 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
18.ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
19.አድራሻ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ (በጌምድር መምህራን ራን ትምህርት ኮሌጅ) ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here