ተጨባጭ የሆነ መፍትሔ ካልተበጀለት
የዋጋ ንረት ጉዳይ በቀጣይም እየጨመረ
እንደሚሄድ የዘርፉ
ባ ለ ሙ ያ ዎ ች
ተናግረዋል፤ አዲስ
ማለዳ ባለሙያዎችን
ጠቅሶ እንደዘገበው
የዋጋ ንረት ተጨባጭ
መፍትሔን ይሻል፤
እንደ ሀገር ያለውን
የፖለቲካ ቀውስ
በማረጋጋት ምርትና
ም ር ታ ማ ነ ት ን
ማሳደግ የሚቻልበት
ሁኔታ ካልተፈጠረ
የዋጋ ንረቱ ጉዳይ
በቀጣይም እየጨመረ
የሚሄድ መሆኑን
የገለጹት የምጣኔ
ሃብት ባለሙያው ዶ/ር
አቡሌ መሃሪ ናቸው::
አምራች የሆነው
ኃይል ከምርታማነት ይልቅ
በግጭት ውስጥ እያሳለፈ መሆኑ ለችግሩ
መባባስ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ እንደሚቀጥልም
አብራርተዋል::
ሌላኛው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዶ/ር አረጋ
ሹመቴ በበኩላቸው ለግሽበቱ መባባስ መንስኤ
በሆኑ ጉዳዮች ላይ መሠራት የነበረባቸው
ሥራዎች ባለመፈጸማቸው ችግሩ እየተባባሰ
መምጣቱን አንስተዋል፤ አቅርቦትን እና
ፍላጎትን የማመጣጠን ተግባርም ከመቼውም
ጊዜ በላይ ትኩረት እንደሚያሻው ተናግረዋል::
በተመሳሳይ የዋጋ ንረቱ ሰዎች በልተው
ማደር የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሷል። በኩር
በጸደጋጋሚ በሠራች ዘገባ ኸሻብ ያካፈሉን
ነዋሪች ይህንን ነው ያረጋገጡት።
ነዋሪዎች እንዳሉት በማንኛም የፍጆታ
ዕቃ ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ይታያል። ከዚህ
በተቃራኒው ደግሞ የዜጎች ገቢ ባለበት ነው።
ይባስ ብሎም በቀን ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ
በግጭቱ ምክንያት ሥራ በመጥፋቱ የከፋ ችግር
ላይ ወድቀዋል።
ሰላም ከተረጋገጠ የዋጋ ንረቱም ሊረጋጋ
እንደሚችል የጠቆሙት ነዋሪዎች ለዚህም
ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል