ፈረንሳይ ስትነሳ ፓሪስ፣ ፓሪስ ስትነሳ ኤይፍል ማማ ይነሳል። 324 ሜትር እርዝመት ያለው ትልቁ ማማ ሙሉ ለሙሉ ከብረት የተገነባ በህንፃ ግንባታ ታሪክ ውስጥ አንዱ የቴክኖሎጂካዊ ፈጠራ ውጤት እንደሆነ ይነገርለታል። በ1881 ዓ.ም ላይ የፈረንሳይ መንግስት የፈረንሳይ አብዮትን መቶኛ ዓመት ለማክበር ዓለማቀፋዊ ኤግዚቪሽን እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት የተሻለ የሀውልት ንድፎችን ለመምረጥ አንድ የውድድር መድረክ አመቻቸ። ከ100 በላይ ንድፎች ለውድድር ቀረቡ፣ እናም የወርቅ ዮቤልዮ በአል አዘጋጅ ኮሚቴው አወዳድሮ ጉስታቭ ኤይፍል የተባለው ታዋቂ የድልድይ መሀንዲስ ያቀረበውን ንድፍ ተቀበሉት። ሦስት መቶ ሜትር ርዝመት ያለው የኤፍልን የንድፍ ሀሳብ አድናቆት፣ ጥርጣሬንም ትችትንም አስተናግዶ ነበር። ይሁን እንጂ ተገንብቶ እንዳለቀ መጀመሪያ ላይ የኤግዚቢሽኑ መግቢያ ሆኖ አገልግሏል። በመጀመሪያ 300 ሜትር ርዝመት የነበረው ሲሆን ከ20 አመታት በኋላ እንደሚፈርስ ነበር የታቀደው።
በ1901 ዓ.ም የመፍረሻ ቀኑ ሲደርስ ለሬድዮ ስርጭት ያለው ጥቅም ከመፍረስ ታደገው ለቴሌቪዥን ማሰራጫነት 24 ሜትር አንቴና ተጨምሮበት ከፍታው አድጎ እነሆ እስከዛሬ ከአለም ድንቃ ድንቅ አንዱ በመሆን ቀጥሏል።
ከአይፍል ማማ ከሶስቱም ደረጃዎች ሆኖ 64 ኪሎ ሜትር እይታን ያስመለክታል። ከማማው መሰረት ዜሮ ነጥብ ስምንት ሄክታር ላይ ሆኖ እስከ ወታደራዊ አካዳሚው ድረስ የተዘረጋው የማርስ መስክ (Field of Mars) ይታያል።
ከሳይን ወንዝ በስተግራ በኩል የተገነባው የአይፍል ማማ ለመሀንዲሱ ክብር በስሙ ተጠርቷል። ሙሉ ለሙሉ በብረት የተሰራ ነው። በመቶ ሽዎቹ የሚቆጠሩ የብረት ቁርጥራጮች ተገጣጥመው የፈጠሩት ይህ ትልቅ ማማ በሮም ካለው የቅዱስ ጴጥሮስ ጉልላት ወይም ከታላቁ የጊዛ ፒራሚድ ሁለት እጥፍ ይረዝማል። በብረት ባህሪያት የጠለቀ እውቀቱን ተጠቅሞ ጉስታቭ ኤይፍል አየር የሚያስገባ፣ ነገር ግን ጠንካራ ማማ አድርጎ ቀርፆታል። በግንቦት ወር 1881 ዓ.ም ላይ ስራው አልቆ ለህዝብ እይታ ክፍት ከተደረገ በኋላ በሚደንቅ ሁኔታ ዉበቱን በራሱ አረጋግጧል።
የማሰራጫ አንቴናውን 5.2 ሜትር ሳያጠቃልል ቪየደክት ቀጥሎ በቁመት ማማ የኤይፍል በፈረንሳይ ምድር ሁለተኛ ረጅሙ ነው። ከምድር ጀምሮ እስከ ጫፍ 300 የመወጣጫ ደረጃዎች አሉት። ከመጀመሪያው ወደ ሁለተኛው ወለል ደግሞ 300 ደረጃዎች፤ በአጠቃላይ 600 ደረጃዎች አሉት።
የአይፍል ማማ ሶስት ደረጃዎች ሲኖሩት በአንደኛው እና በሁለተኛው ደረጃዎች ላይ ለጎብኝዎች የሚያገለግሉ ሬስቶራንቶችን ይዟል። ሶስተኛው ወለል አነስተኛ መኖሪያ ያለበት ነው። በዚህ ድንቅ የዘመናዊ ምህንድስና ውጤት በሆነው የአይፍል ማማ ከስር ጀምረን እስከ ላይ ያሉትን ክፍሎች እየጎበኘን በአሳንሰር አየተንሸራሸርን የተለያዩ የማማውን ክፍሎች እንዲሁም ከርቀት እይታውን እየኮመኮን አብረን እንጓዛለን።
የአይፍል ማማ የምድር ክፍሉን በማየት ስንጀምር በመጀመሪያው የምናገኘው የማማውን መሰረት ነው። አራቱም ምሰሶዎች አሳንሰሮች ወደ መጀመሪያዎቹ ሁለት ፎቆች ለማጓጓዝ ዝግጁ የሆኑ አሳንስሮች ይዘዋል። ካልፈለጉም በእግር መሄድ የሚያስችሉ የመወጣጫ ደረጃዎች አሉት።
በአንደኛው ፎቅ አረፍ ማለት ከፈለጉ ሦስት የተለያዩ ሬስቶራንቶች አሉ። አንድ የፈረንሳይ፣ አንድ የራሺያ፣ እና አንድ የፍሌሚሽ እንዲሁም የእንግሊዝ እና አሜሪካ ባር አሉ። ኤክስፖው ከተጠናቀቀ በኋላ የፍሌሚሽ ሬስቶራንቱ ወደ ባለ 250 መቀመጫ ያለው ሲኒማ ቤትነት ተቀይሯል። በአሁኑ ወቅት በርካታ ዘመናዊ የአገልግሎት ማእከላትን አካቷል።
ሁለተኛው ፎቅ ሌላው የማማው ክፍል ሲሆን በአሳንሰር ወይም በእግር መድረስ ይችላሉ። ማንኛውም ሰው ሊገባ ይችላል። በዚህ ለ ከልስ ቨርን የተሰኘ አንድ ሬስቶራንት አለ። ሬስቶራንቱ ከማማው ደቡባዊ ምሰሶ በቀጥታ የሚመላለስ የራሱ አሳንሰር ያለው እና ስያሜውንም ከእውቁ የሳይንሳዊ ልብ ወለድ ፀሀፊው ስም የተወሰደ ነው።
ወደ ሦስተኛው ፎቅ እያመራን ነው። ከጫፍ ያለው ፎቅ ሲሆን በአሳንሰር ብቻ ነው መጓዝ የሚቻለው። መጀመሪያ ላይ ለተለያዩ ምርምሮች የሚሆኑ ቤተሙከራዎች እና ለጉስታቭ ኤይፍል የእንግዶች መቀበያነት አንድ አነስተኛ መኖሪያ ቤት ሆኖ ያገለግል እንደነበር ይነገራል። በውስጡ ዘመኑን በሚያስቃኙ ማስዋቢያዎች እና በህይወት ያለ የሚመስል የኤይፍል ሀውልት ተሟልቶለት አሁን ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይጎበኛል።
ፓሪስ በሁሉም አቅጣጫ እስከ 64 ኪ.ሜትር ራዲየስ ያለውን ርቀት ወይም አካባቢ ማየት ይቻላል። በየአመቱ ከሰባት ሚሊየን በላይ ጎብኝዎች እንደተመለከቱት የሚነገርለት አይፍል ማማ፣ ከተጀመረበት እስካሁን ከ250 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎች እንደተመለከቱት ብሪታኒካ ያሳያል።
(መሰረት ቸኮል)
በኲር የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://