በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ ውል ለተኝቶ ህክምና ታካሚዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የበሰለ ምግብ
አቅርቦት በሆቴሎችና ካፍቴሪያ ዘርፍ ፈቃድ ላላቸው ግለሰቦች (ማህበራት) እና ሎት2. የጭነት አገልግሎት ማለትም የኦክስጅን ስሊንደር አሰሞልቶ ማስመጣት እና ልዩ ልዩ
መድሃኒቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጫን እና ለምግብ ተጫራቾች ደግሞ የሆስፒታሉን ካፍቴሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ ማከራየት እና ማስቀረብ ይፈልጋል::
በካፌው የሚቀርቡ አገልግሎቶች
1. የምግብ ከፋስት ፉድ ጀምሮ የተለያዩ ምግብ አይነቶችን::
2. የተለያዩ ትኩስ መጠጦች የጀበና ቡናን ጨምሮ::
3. የተለያዩ ቀዝቃዛ መጠጦችን ከአልኮል ወጭ::
4. መቀመጫ ወንበር እና ጠረጴዛ ማቅረብ የሚችል
5. የሻይ ማሽን፣ ፍሬጅ፣ ቴሌቨዝን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን አሸናፊው ተጫራች የሚያቀርቡ ሲሆን ተጫራቶች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው::
2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው::
3. የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ
የሚችሉ::
4. ተጨራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ
ማቅረብ አለባቸው:: ነገር ግን ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ያላቀረቡ ተጫራቶች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ::
5. የሚቀርቡ የምግብ እና የመጠጥ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኝት ይችላሉ::
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 30.00 /ሠላሳ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ማግኝት ይችላሉ::
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲቢኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ
ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ::
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአስራደ ዘዉዴ መታሰቢያ
መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቡሬ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15
ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 3፡59 ድረስ ማስገባት ይችላሉ::
9. ጨረታው ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራደ ዘውዴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን
ጀምሮ በግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል:: የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት
ይሆናል::
10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጨራቾች ላወጡት ዋጋ
ሆስፒታሉ ተጠያቂ አይሆንም::
11. የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ
ውል መያዝ ይኖርበታል::
12. ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት 10.000.00 /አስር ሽህ ብር/ እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ሁለት በመቶ ይቀነሳል::
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ
ቁጥር 058 774 0576 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል::
14. የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረተበት ዘርፍ በጥቅል ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን በመምረጥ ነው::
15. የጭነት አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም::
16. ለሎት2. የጭነት ተወዳዳሪዎች ሙሉ ወጭውን ማለትም እንደ ናፍጣ እና ጫኝ አውራጅ ያሉትን በራሳቸው ወጭ ሸፍነው መድሃኒቱን እና የኦክስጅን ስሊንደሩን ቡሬ
ሆስፒታል ግቢ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርባቸዋል::
17. ከ3,000.00 /ሦስት ሽህ ብር/ እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ሁለት በመቶ ይቀነሳል::
18. ጨረታው ከሆስፒታሉ ባዶውን ሲሊንደር ጭኖ ወስዶ ባሕር ዳር አስሞልቶ አስወርዶ ያለውን ሂደትም ይጨምራል::
ማሳሰቢያ
• ተጫራቾች የካፌውን እና የተኝቶ ታካሚዎችን ምግብ ተለይቶ መሞላት አለበት
• የካፌው ወርሀዊ ኪራይ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ሆኖ የሚቀርቡ ምግብ እና መጠጦች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መሆን አለበት::
• መብራት እና ውሃ በሆስፒታሉ ካለ የሚቀርብ ሆኖ ሆስፒታሉ በማይኖርበት ጊዜ አሸናፊው ገዝቶ የሚጠቀም ይሆናል:: ተጫራቶች ለካፍቴሪያው ከተዘረዘሩት
የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች በተጨማሪ ከአልኮል ውጭ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ::
የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል