ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን/ጎ/ዞ በደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ ዓመታዊ ግዥ ለመፈጸም ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የፅዳት ዕቃ፣ ሎት 3. የኤሌክትሪክ
እቃ፣ ሎት 4. ህትመት እና ሎት 5. የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች (ተጫራቾች)
መሳተፍ ይችላላችሁ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ጨምሮ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የጨረታ ሰነዱን ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ዝርዝር መረጃ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ
ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በየምድቡ (በየሎቱ ) በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሽግ ደ/
አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
9. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ
ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ በተላለፉት ውሣኔዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ ይሆናል፡፡ የመክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ
የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
10. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸበፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ
ይኖርበታል፡፡ በተባለው ቀን ውስጥ ውል የማይዝ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል፡፡
11. ጨረታው የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም የተጠየቀውን እስፔስፊኬሽን በራሡ መቀየር
አይቻልም፤ ስርዝ ድልዝ የበዛበት መሆንም የለበትም፡፡ በስህተት ከተሠረዘ በማያጠራጥር ሁኔታ ፓራፍ ማድረግ አለበት፡፡
12. አሸናፊው ያሸነፈባቸውን እቃዎች የማውረጃ እና የማስጫኛ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪውን ችሎ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብና ንብረት ክፍል ማስረከብ
ይኖርበታል፡፡
13. የሠነድ መሸጫ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት 50.00 (ሀምሣ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
14. መሥሪያ ቤቱ ባወጣው ጨረታ ላይ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
16. ሁሉም ተጫራቾች የግዥ ደንብና መመሪያን ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በአካል ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በስልክ 058 223 07 52 መጠየቅ ይችላሉ፡
የዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል