ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
181

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን G+0 የሆነ የህፃናት ማቆያ ህንፃ ለማስገንባት እስከ ማጠናቀቂያ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና ቁሳቁስ ያካተተ የቴክኒክና የፋይንሻል ፕሮፖዛል ወይም የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- ለGC-5/ BC-5 እና ከዚያ በላይ ለሆናችሁና በ2016 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድና የሥራ ፈቃድ እንዲሁም የግንባታ ሥራ አገልግሎት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ለምትችሉ ተቋራጮች በሙሉ፡-

  1. ተጫራቾች የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በባንክ ወይም በአካል ጥሬ ገንዘብ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአብክመ ሲ.ሰ.የሰ.ኃ.ል.ኮ ቢሮ ቁጥር 007 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላውን የመጫረቻ ዋጋ ሁለት በመቶ ከታወቁ ባንኮች ሲፒኦ (በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በፋይናንስ ተቋም የተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ከፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የመጫረቻውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
  5. ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን ሙሉ በሙሉ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. የግንባታ ሥራው ከተጀመረበት ቀን አንስቶ በ255 የመቁጠሪያ ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በነፃ የገበያ ዋጋ ላይ ተመስርተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የሚቀርቡት የመጫረቻ ሰነዶች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ተለይተው አንዳንድ ኦርጅናልና አንዳንድ ቅጅ ተደርገው በተለያዩ ፖስታዎች (ኤንቨሎፕ) ታሽገው የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
  9. የቴክኒካል መመዘኛ መሥፈርቱን 70% እና በላይ ያላመጡ ተጫራቾች ቅድመ መሥፈርቱን እንዳላሟሉ ተቆጥሮ ከውድድር ውጭ የሚሆኑ ሲሆን የፋይናንሻል መጫረቻ ሰነዳቸው ሳይከፈት ይመለስላቸዋል፡፡
  10. የቴክኒክ መሥፈርቱን 70%እና በላይ ያሟሉ ተጫራቾች ወደ ፋይናንሻል ውድድር እንዲያልፉ ያደረጋል፡፡
  11. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 የመቁጠሪያ ቀናት ውስጥ በሚኖሩት የሥራ ቀናት ከ2፡30-11፡30 በአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን በቢሮ ቁጥር 007 በር ላይ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የመቁጠሪያ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የሥራ ዕድል አማራጮችን ለማስፋትና ለማበረታታት በወጣው የገበያ ትስስር ፈጠራ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 52/2014 አንቀጽ 10 መሠረት ከሚወስደው ሥራ ውስጥ ቢያንስ አስራ አምስት በመቶ በግንባታ ሥራ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ መስጠት ይኖርበታል፡፡
  14. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  15. ተጫራቾች ከዚህ ቀደም በያዟቸው የግንባታ ውሎች መሠረት ያከናወኗቸውን ተግባራት የሚገልጽ የሥራ ልምድ ወይም የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  16. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተገለጹት ዕቃዎች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  17. ኮሚሽኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው፡፡
  18. ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 ወይም 058 220 96 46 ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  19. ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ በ”PDF” የተዘጋጀ በመሆኑ የጨረታ ሰነዱን የሚገዙ ተጫራቾች ሙሉ ዶክመንቱን በፍለሽ መውሰድና ማንበብ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ማስታወቂያውና የዋጋ መሙያው ግን በሐርድ ኮፒ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

 

የአብክመ ሲቪል ሰርቢስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here