በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ት/ት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የግንባታ ማቴሪያል ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በየዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ እና አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው አስር በመቶ የውል ማሰከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚይወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በየሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከ09/07/2016 እስከ 23/07/2016 ዓ/ም በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ 11፡30 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑን በ24/07/2016 ዓ/ም 9፡00 ታሽጎ 9፡30 ሕጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ /ካላደር ከሆነ/ በቀጣዩ የሥራ ቀን 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡30 ሕጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው በየዳ ወረዳ ሲ/ሰ/ፑል ማስረከብ የሚችል እና የማውረጃ እና መጫኛ በራሱ መሸፈን የሚችል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታው ማህተም ከንግድ ፈቃዱ ጋር ቀጥተኛ /ተዘማጅ የሆነ መሆን አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 09 1835 22 28 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡