ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
154

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር  ፍ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መሥሪያ ቤቱ ባወጣው ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. በዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅርብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ኮፒውን እና የዋጋ መሙያቸውን ኦርጅናል በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. የሰነዱን ዝርዝር መግለጫ ከደ/ማ/ከ/አስ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት ከዋና ገ/ያዥ 50.00 /አምሳ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 05 79 24 እና 09 23 23 26 74 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ጠቅላላ ዋጋ 0.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ሃሣቡን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በደ/ማ/ከ/አስ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፤ ጨረታው በ16ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ አስር በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውን ፣ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች የሚሰጧቸውን የመጫረቻ ዋጋዎች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ያልተመሰረቱ መሆን አለባቸው፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ ከተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቹ የሞላውን ዋጋ ሳይለውጥ ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች ደ/ማ/ከ/አስ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here