የሻላ ሐይቅ በጥልቀት እንዲሁም በውሃ ይዘት መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሐይቆች የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል።
ሐይቁ በዋናው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ይካለላል። ከባህር ወለል በላይ አንድ ሺህ 559 ሜትር ከፍታ አለው። ከአዲስ አበባ በስተደቡብ፤ በሞያሌ መንገድ 225 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
የሐይቁ ርዝመት 27 ኪሎሜትር፤ አጠቃላይ ስፋቱ ደግሞ 314 ኪሎሜትር ስኩዌር ነው። የሻላ ሐይቅ ጥልቀት 266 ሜትር ሲሆን በተደጋጋሚ የሚከሰተው ጥልቀት ደግሞ 86 ሜትር ነው።
ሐይቁ የሚይዘው የውሃ መጠን 38 ቢሊዮን ሜትር ኩብ እንደሆነ ይገመታል። ይህ የውሃ መጠን በሌሎቹ የኢትዮጵያ ሐይቆች ማለትም ጣና፣ ዝዋይ፣ አብያታ፣ ላንጋኖ እና የአዋሳ ሐይቆች በአንድ ላይ ሆነው ከሚይዙት የውሃ መጠን እጅግ የላቀ ነው።
ምንጭ፦ www.wikimapia.org
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም