የተባበሩት መንግሥታቱ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ17 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ መመደቡን አስታውቋል፤ በድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ በኢትዮጵያ እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የ17 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ነው የተናገሩት።
የገንዘብ ድጋፉም በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ ተጎጂዎችን ለመታደግ ያስችላል ተብሏል። ይን እንጂ ኢትዮጵያን የገጠመው የምግብ ዋስትና እጦት እየበረታ ሊሄድ እንደሚችል ስጋቱን አስቀምጧል።
ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ጦርነት እና ሌሎች ግጭቶች ኢትዮጵያዊያንን ለከፋ ችግር ማጋለጡን ድርጅቱ በድረ ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ አመላክቷል።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ እያሻቀበ ላለው የተረጂዎች ቁጥር ሦስት ነጥብ አራት ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ያስፈልጋል ተብሏል፤ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለለ አቡሃይን ጠቅሶ አል አይን እንዳስነበበው፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው የተረጅዎች ብዛት ስድስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ደርሷል፤ በጎርፍ እና በሌሎች ምክንያቶች አኀዙ እንደሚጨምርም አክለዋል።
(ጌትሽ ኃይሌ)
በኲር መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም