ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
156

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ ዓመታዊ የቢሮ ፅዳት አገልግሎት ግዥ እና የተለያዩ የፋይናንስ ህትመቶችን ግዥ ለመፈጸም  በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅት ማሟላት ያለባቸው፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ የእቃው /የአገግሎቱ ግዥ መጠን ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (ለአስራ ምስት) ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት  ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ  ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ  የማይመለስ 150.00 (አንድ መቶ አምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን  መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ  የድርጅቱን ሕጋዊ  ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመሥሪያ ቤቱ  ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የመጫረቻ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኝው አብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡
  4. በመሆኑም በዕለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16 ተኛው (በአስራ ስድስተ ኛው) ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋልና ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት እቃ /አገልግሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
  7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የቢሮ ፅዳት አገልግሎት ግዥ የምትወዳደሩ ድርጅቶች ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ለበለጠ ግልፅነት ይረዳችሁ ዘንድ በአካል በመምጣት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻልን፡፡
  9. የሚገዙ እቃዎች /አገልግሎቶች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፤ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይቻላል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here