ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
154

ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የጽሕፈት መሣሪያ እና የዋይፋይ እቃዎች  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ  ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለጽሕፈት መሣሪያ ለሚወዳደሩበት 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ እና ለዋይፋይ እቃዎች ለሚወዳደሩበት 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ከ 16/07/2016 እስከ 30/07/2016 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን በ01/08/16 ዓ.ም 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፍትህ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here